Saturday, November 15, 2014

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ የሚኖሩ ወገኖቻችን ሃላፊነት የጎደለውን የስርዓቱ አካሄድ በመቃዎማቸው እየታሰሩ እንደሚገኙ ተገለፀ፣






   ለችግሩ ሰለባ የሆኑትን መሰረት በማድረግ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች በኢሮብ ወረዳ ሓራዛ ስብዓታ ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን ህዝብ ጥቅምት 14/2007 ዓ.ም ሰብስበው በዓሲምባ አካባቢ እንደተካሄደና፤ በዚህ አካባቢ በሚገኙ ዕንዲፊ፤ ካሶማለ፤  አላሂቶን፤ ያሆዳጋን በተባሉት ቀበሌዎች የሚኖሩ ወገኖቻችን ያለምንም ካሳ እንዲፈናቀሉ እንደተወሰነና፥ ስብሰባውን የመሩትም፦
·     ዓስቦም ካሕሳይ የወረዳው ፈፃሚና የወጣቶች ሊቀመንበር፤
·     ምክትሉ ፍሱህ ግደይ የእርሻ ባለሙያ፤
·     አለማ ብሩ የወረዳው የፕሮፖጋንዳ ሓላፊና ወልዱ ሓጎስ በህዝቡ ፊት ቀርበው በሚናገሩበት ሰዓት ተሰብሳቢው ህብረተሰብ ሙሉ በሙሉ ውሳኔውን ውድቅ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፣
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በነበረው መድረክ ላይ ህዝቡ ባስነሳው ተቃውሞ የተቆጡት የስርዓቱ አመራሮች ካሰሯቸው ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ፦
·     የውሃንስ ዕመር የሓራዛ ቀበሌ የፕሮፖጋንዳ ሃላፊ፤
·     ፍሰሃየ መድህን የስብዓታ ቀበሌ ስራ አስኪያጅ፤
·     አለም አሰፋ የቀጠነዋ ፀሃፊ፤
·     ሓዲሽ ሓጎስ የቀጠናው ተወካይ፤
·     አብርሃ ስብሓትና ንጉሰ አብርሃ የቀበሌ ህዝብ ግንኙነት፤
·     ስዩም ስሙር የቀበሌ ልማት ቡድን ሓላፊና ሌሎችም የሚገኙባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፣