Pages

Saturday, November 15, 2014

በአፋር ክልል የሚገኙ የገዠው ስርዓት ሰራዊት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የማስፈራራትና የማናናቅ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ከአካባቢው የደርሰን መረጃ አመለከተ፣




   በመረጃው መሰረት በአፋር ክልል በራሕለ ወረዳ ባዳ ቀበሌ የሚኖሩ ዜጎችን፤ በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጂመንት በሆነው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሰራዊት ግፍ እየተፈፀመባቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው፤ በዚህ ሳቢያም ነዋሪዎቹ በአካባቢው የሰፈረው  ሰራዊት ይውጣልን በማለት ጥቅምት 26 ቀን 2007 ዓ/ም ከፍተኛ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ታውቋል፣
    በተማጨማሪም የባዳ ነዋሪዎች በተቃውሞው እያሰሙት ከነበረው መፈክር የተወሰኑትን ለመጥቀስ፤ ባህልና ወጋችንን እያበላሹ ያሉት የገዥው ፓርቲ ወታደሮች ከአካባቢያችን ይውጡልን፥ ወታደሮች እንደወገኖቻቸው አያዩንም፥ በላያችን ላይ የጥላቻ መንፈስ አላቸው የሚሉና ሌሎችም መሆናቸውን የገለፀው መረጃው። በአስተዳዳሪዎች በኩል ግን እናስተካክለዋለን ከማለት በስተቀር በተግባር ሲያስተካክሉ  አልታዩም በማለት ነዋሪዎቹ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ እየገለፁ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስረድተዋል፣