Wednesday, June 10, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ የግንቦት 20 ድል ያመጣቸው ፍሬዎች ምን ይመስላሉ በሚል የቀረቡ ቃለመጠይቆች በህዝብ ተቃውሞ እንደገጠመው ለማወቅ ተችሏል።



    ከስፍራው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለከተሞች ከአምባገነኑ የኢህአዴግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት የተበተነው የግንቦት 20 ድል ያመጣቸው አንፀባራቂ የፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና መልካም አስተዳደራዊ ፍሬዎች በእርስዎ እይታ ምን ይመስላሉ በሚል የቀረበውን ቃለመጠይቅ አጠቃላዩ ህዝብ የተቃወመው ሲሆን በተለይ በመጠይቁ ላይ ከተቀመጡት  የዜጎች እኩልነት፤ የዲሞክራሲያዊ መብት አሰጣጥና አያያዝ፤ የጤና ተኮር ስራዎች፤ የፖለቲካ ምህዳር ማስፋት፤ የሃገሪቱ እድገትና የሁለት አሃዝ ማስመዝገብ የሚሉትን በእያንዳንዳቸው ፊት ለፊት 0 (ዜሮ) መቀመጡ በለጋሃር የባቡር ጣቢያ ስር በሚገኘው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ቃለመጠይቅ ዋቢ በማድረግ  በአንክሮ አስረድተዋል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለም የአዲስ አበባ ህዝብ የሰማያዊ ፓርቲን መርጠን እያለ ገዥው መንግስት ድምፃችንን አጭበረበረን በማለት እየተቃወሙ ሲሆን በተለይ በሰንዳፋ አካባቢ ሰንዳፋ በተባለው ምርጫ ጣቢያ ለምርጫ ከተመዘገበው 1200 ሰው 410 ብቻ የመረጠ ሲሆን ሌላው ህዝብ ግን ለምርጫ አለመውጣት አንድ ራሱን የቻለ ተቃውሞ መሆኑን መንግስት ይወቅ በማለት ራሳቸውን ያገለሉ ሲሆን ገዥው መንግስት ተመረጥሁ ማለቱም እንዳስቆጣቸው ተናግረዋል።