Pages

Wednesday, June 10, 2015

በአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች በቅርቡ የተካሄደውን የ2007 ዓ/ም የምርጫ ውጤት አንቀበልም በማለት ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።



    በቅርቡ በተካሄደው ሃገራዊ የይስሙላ  ምርጫ ላይ የተሳተፉ የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች እኛ የመረጥነው ይወክለናል ያልነውን የሰማያዊ  ፓርቲ መርጠናል ስለዚህ በምርጫችን መሰረት ውጤቱ መምጣት አለበት በማለት ነዋሪው ህዝብ ተቃውሞውን እያሰማ መሆኑን የገለፀው መረጃው በምርጫው ሰዓትም አንዳንድ የግንዛቤ እጥረት ያለባቸውን ሴቶችንና አረጋዊያንን የስርኣቱ ካድሬዎች  ታዛቢዎችን እንደምንም ባለመቁጠር ወደ ምስጢር የድምፅ መስጫ ጣቢያው ድረስ በመግባት በንብ ላይ ምልክት አድርጉ በሚል ያሳሳቱ መሆናቸውን አስረድተዋል። 
   የምርጫ ውጤታችን በምርጫችን መሰረት ሊመጣልን ይገባል። እኛ ራሳችንን በራሳችን እያስተዳደርን እንጂ ከመንግስት የተደረገልን ምንም ዓይነት የመሰረተ ልማት ድጋፍና እገዛ አለመኖሩን መንግስት ያውቃል ስለዚህ አልመረጥነውም በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ከሚገኙት  መካከል በባህርዳር የቀበሌ 10 ነዋሪዎች እንዲሁም  የቡሬ ወረዳ ቁጪ 01 እና የሶንቶም ቀበሌ ነዋሪዎች መሆናቸውን ምንጮች አስረድተዋል።