ምንጮቻችን እንደገለፁት በትግራይ ምስራቃዊ
ዞን ኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ አካባቢ የሚገኙ የዓረና/መድረክ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት የሆኑት አቶ ልኡል አድሓኖም ብስራት የተባሉት
ወገን ግንቦት 17/2007ዓ/ም ጥዋት ላይ የምርጫ ውጤት ለመታዘብ ወደ ምርጫ ጣቢያው አምረተው ውጤቱን አይተው ባለመቀበላቸው የተነሳ
ህዝብ የሰጠውን ድምፅ ለምን አታከብርም በማለት ሰዎችን ወደ አልተፈለገ መንገድ እንዲያመሩ ትቀሰቅሳለህ በሚል ምክንያት ግንቦት
22/2007ዓ/ም ወደ ዓዲግራት እስር ቤት ወሰደው እንዳስሯቸው ለማወቅ ተችሏል።