Wednesday, June 10, 2015

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ከምርጫ በኋላ ዜጎች ያለምክንያት እየታሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።



   የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ከምርጫ ማግስት ጀምሮ በተሰማሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተላላኪ  የደህንነት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተሞች ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድም በማለት ንፁሃን ዜጎችን እያሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።  
   በክልሉ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል  ቶንጎ ወረዳ ጦጦራ ቀበሌ ነዋሪ የነበረ ለጊዜው ስሙ በወል ያልታወቀ የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ የ19 ዓመት ወጣት ግንቦት 24 ቀን 2007 ዓ/ም ከአሸባሪዎች የተላከ በሚል የሃሰት ውንጀላ ገዥው መንግስት ባሰማራቸው ተላላኪዎች እጆቹ ወደ ኋላ ታስሮ አሶሳ ወደሚገኘው ከፍተኛ ማረሚያ ቤት መወሰዱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።