Pages

Friday, September 4, 2015

የሰባት ዓመት አገልግሎታቸው የጨረሱ ወታደሮች በሚል ሰበብ ያልተፈለጉትን ለማሰናበት የቀረበውን ሃሳብ አጠቃላይ ሰራዊቱ አሰናብቱን የሚል ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት ፈጥረው ሁኔታውን እንዳስቆሙት ተገለጸ።



    ከመከላከያ ሰራዊት የደረሰን መረጃ እንዳስረዳው ከነሓሴ 14/2007 ዓ/ም ጀምሮ በየክፍሉ እየተካሄደ የሚገኘውን ስብሰባ እንደ አንድ መነጋገርያ አርእስት ሆኖ የቀረበውን ሃሳብ 7 ዓመት ያገለገሉት ወታደሮች ሊሰናበቱ እንደሆኑ ቢገለፅም ከ 7 ዓመት በላይ ያገለገሉት ወታደሮች ሊሰናበቱ ከሆነ ያለምንም ልዩነት ለሁላችንም አሰናብቱን የሚል ጥያቄ በመነሳቱ ምክንያት በተፈጠረው ሁኔታ የተደናገጡት የመድረኩ መሪዎች ሌላ አርእስት በመቀየር የተነሳውን ሃሳብ ሸፋፍነውት እንዳለፉ ለማወቅ ተችሏል።
   ሊፈጸም የታሰበውን የስንብት ሁኔታ በጥርጣሬ አይን የሚታዩትን ወታደሮች አስመልክቶ ቢሆንም በአጠቃላይ በሰራዊቱ የቀረበውን አሰናብቱን የሚል ጥያቄ ሸፋፍነውት ለማለፍ ቢሞክሩም ሰራዊቱ ግን ጥያቄው በተገቢ መንገድ መመለስ አለበት ካልሆነ በተመቸን ግዜና ቦታ በራሳችን ግዜ እንደምንሄድ ማወቅ ይገባችኋል በማለት በግልፅ እንደተናገሯቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።