Friday, September 4, 2015

በነቀምቴ ከተማ መኖሪያ ቤቶች በዶዘር አፍርሰው ለኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ እንዲሰጡ የተላኩት የስርአቱ ተላላኪዎች በነዋሪው ህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ተገለጸ።



    በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የድሆችን ቤት በመለየትና መሬቱን ለድያስፖራዎች ለመስጠት በተዘጋጁበት ግዜ ነዋሪዎቹ ዛሬ ይሁን ነገ አንወጣም በማለታቸው ምክንያት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ተላላኪዎቻቸውን በማሰማራት ነሃሴ 13/2007 ዓ/ም በዶዞር ለማፍረስ በሞከሩበት ሰዓት ፋይሳ ነይስ የተባለ የፖሊስ ግብረ-ሃይል  አስተባባሪ በከፍተኛ ሁኔታ መቁሰሉ ታውቋል።
    ሃላፊነት በሌለው የመኖርያ ቤት መፍረስ የተጎዱት ነዋሪዎች የሚኖሩበት ቤት ስለሌላቸው በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙና የአካባቢው ማህበረሰብም ከጎናቸው ጋር ሆኖ የስርአቱ ተላላኪዎችን ለማባረር መሞከሩን የገለጸው መረጃው በወቅቱም 10 የሚያህሉ መኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸውና የተፈፀመውን ድርጊት ያልተቀበለው ኢብራሂም የተባለ የአንድ ቀበሌ አስተዳዳሪም በራሱ ከሃላፊነቱ መልቀቁን መረጃው አክሎ አስረድቷል።