Tuesday, December 8, 2015

በወልቃይት ወረዳ ቆራሪት ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃይ ለሆኑ ገበሬዎች መቋቋምያ ተብሎ የመጣ ገንዘብ የኣካባቢው ኣስተዳዳሪዎች እያቀናነሱ ለግል ጥቅማችው እያዋሉት መሆናቸው ምንጮቻችን ገለፁ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በምእራባዊ ዞን ትግራይ ወልቃይት ወረዳ ቆራሪት ከተማ በህዳር 10 2008 አ/ም ስርአቱ  መሬታቸወን ነጥቆ ያፈናቀላቸው ገበሬዎች መቋቋምያ እንዲውል ታስቦ በብዙ አቤቱታና ጥረት የተገኘው 37 ሺ ብር ጫቅለ  ተስፋይና ፀጋይ ፍትዊ የተባሉ የኣከባቢው ኣስተዳደሪዎች ገንዘቡ እየቆረጡ በማስቀረትና የት እንደዋለ ሳይታወቅ በማትረፍ የተወስነውን ብቻ ለማሰመስል እንዳከፋፈሉት ታወቀ።
      ለተፈናቀሉ ገበሬዎች ማቋቋምያ ተብሎ ከመጣው 37 ሺ ብር  ከያንዳንዱ ተፈናቃይ ገበሬ የተቀነሰው 10 ሺ ብር ስለምንና? ለምን? ተቀንሶ 27 ሺ ብር ብቻ  የታደለው በማለት ህዝቡ  ጥያቄውን በማቅረብና ኣስቸኳይ ምላሽም  እንዲሰጠን" ኣለበለዚያ   እስከ ፈደራል ድረስ በመሄድ ኣቤቱታቸና ጥያቄዎች እናቀርባለን በማለት ተቃውሞ ማንሳታቸው ለማወቅ ተቻለ።