መረጃው እንደሚያመለክተው፣በኢትዮጵያ 108 የሚሆኑ የውስጥና 14 የሚሆኑ
ደግሞ የውጭ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ፈቃዳቸውን እንደተቀሙና ሌሎች 167 ተቋሞች ደግሞ በፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰኔ 21 ቀን
2008ዓ/ም በተጠራው ስብሰባ እንደታዘዙ ለማወቅ ተችሏል።
የግብረ
ሰናይ ድርጅቶች ግንኙነት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አሰፋ ተስፋይ እንዳሉት አብዛኞቹ የተጠሩት ተቋሞች በበጀት እጥረት ምክንያት
እንደሆነ ሲገልፁ፣ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለረጅም ጊዜ ምክር በመስጠት የሚሰሩ የህግ ባለሙያ አቶ ደበበ ኃይለ ሚካኤል በበኩላቸው
ከሰጡት ሃሳብ ደግሞ ተቋማቱ እንዲዘጉና እንዲዳከሙ ምክንያት የሆነ ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተብሎ የወጣ ህግ፣ ህጉን የሚፈፅሙ ሰራተኞችና
ኤጀንሲው በመጣሳቸው ነው በማለት የየራሳቸውን የተለያየ ምክንያት እንደሰጡ ለማወቅ ተችሏል።
በመጨረሻም
የውስጥና የውጭ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ፍቃዳቸውን እንዲቀሙ የተደረገበት ምክንያት፣ በበጀት እጥረት ወይም ደግሞ ከመምሪያ ውጭ ስለሄዱ
ሳይሆን፣ በአገሪቱ ላይ እያጋጠመ ያለውን የዜጎች የሰብአዊ መብት ጥሰትና እለታዊ ግጭት በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የሚያዩትን እውነተኛ ሁኔታ ለሦስተኛ ወገን አሳልፈው እንዳይሰጡ ሆን ተብሎ
የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ የተለያዩ ወገኖች በመግለፅ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment