Pages

Sunday, January 5, 2014

በባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ የበላይ ባለስልጣኖች ለልማት እየተባለ የሚሰበሰበውን የሃገርና የህዝብ ገንዘብ እያጠፋፉት መሆናቸው ከከተማው የተገኘው መረጃ ገለጸ፣




በተለያዩ ያኣገራችን ክልሎችየሚገኙ የኢህኣዴግ ባለስልጣኖች የሀገርና የህዝብ ገንዘብ በመዝረፍ ስራ ላይ እንደተሰማሩ የገለፀው መረጃው በባህርዳር ከተማም በህዳር 15/2006 ኣ/ም በተደረገው ስብሰባ ለመሰረተ ልማት ግንባታ ተብሎ ከህዝቡ ብተዋጣው 400 ሺ ብር በክልሉ ባለስልጣናት እንደተጠፋፋ ለማወቅ ተችለዋል፣
     ይህንኑ ከላይ የተገለፀው መጠን ያለው የህዝብ ገንዘብ ካጠፋፉ የስራኣቱ የበላይ ኣመራሮች ውስጥ የከተማው ከንቲባ ኣቶ ሊቆው ኣያሌውና የፀጥታ ሃላፊው ኣቶ ደረሰው ታመነ እንደሆኑና ገንዘቡን ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው የተረጋገጠ መሆኑ ቢታወቅም የስርኣቱ ቀኝ እጅ በመሆናቸው ምክንያት እስካሁን በላያቸው ላይ የተወሰደ እርምጃ እንደሌለ የተገኘው መረጃ ኣስታወቀ፣
    ከዚሁ ከተማ ሳንወታ ኣኣሁንም በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ሰራተኞች ስልጣን ላይ ያለውን ስራኣት በመቃወም ከታህሳስ 11/2006 ኣ/ም ጀምሮው በተከታታይ ለ4 ቀናት ስራ የማቆም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ የገለፀው መረጃው የተቃውሞው ሰልፍ ዋና ምክንያትም መንግስት ስልጣን ለወጣቱ ትውልድ እናስተላልፈዋለን ባለው ቃል መሰረት ሊሄድበት እንዳልቻለና ይባሱን ከ55 ኣመት እድሜ በላይ ለሆኑ ሰዎች ለስልጣን እያበቃቸው ነው በሚል ምክንያት ኣንደሆነ መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣