እነዚህ በጎንደር ኣካባቢ የሚገኙ የትክል
ድንጋይ ነዋሪ የሆኑ ዜጎቻችን በከተማው ውስጥ ባለው የመሰረተ ልማት እጥረት ምክንያት እለታዊ ንሮኣቸው በመምራት ላይ ከባድ ችግር
ውስጥ ወድቀው እንዳሉ የገለፀው መረጃው፤ በተለይ በንፁህ ውሃ እጥረት እጦት ምክንያት ብዙዎች ህፃናቶችና ኣዛውንቶች የሚገኙባቸው
ዜጎቻችን ለበሽታ እየተጋለጡ መሆናቸውና ከነዚህም ህፃን ሰላም ታፈረና ኣቶ ታፈረ ታደሰ የተባሉ ወላጅ እንዲሁም ሌሎች በርከት ያሉ
ነዋሪዎች የችግሩ ሰለባ እንደሆኑ ይህክምና ባለሞያዎ ዋቢ በማድረግ ያገኘነው መረጃ ኣስረድተዋል፣
ለዚሁ ኣጋጥሞ ያለው የመሰረተ ልማት እጥረት መፍትሄ እንዲደረግላቸው ነዋሪዎችዱ
በታህሳስ 17/2006 ኣኣ/ም ሰላማዊ ሰልፍ ቢያካሂዱም በዚሁ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የተደናገጡ የስርኣቱ ባለስልጣናት ተገቢ ስመልስ
ከመስጠት ይልቅ ፖሊስ በተቃዋሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ማውረዳቸው ስራኣቱ ምን ያህል ከህዝቡ ርቆ ኣንዳለ የሚያረጋግጥ
መሆኑንና። በሚጠጣ ንፁህ ውሃ እጥረት ምክንያት የሚታመምና የሚሞት ኣንዳች ዜጋ የለም እያለ የሚናገረው ከንቱ ፕሮፖጋንዳ ከሃቅ
የራቀ ነጭ ውሸት መሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ጨምረው ገልፀዋል፣