Tuesday, January 7, 2014

የትግራይ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት ሃላፊ የሆነው ግለሰብ ለፅህፈት ቤቱ ስራ ማስከጃ ተብሎ የተመደበ በርከት ያለ ገንዘብ ይዞት እንደተሰወረ ተገለጸ፣




መቀሌ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የክልሉ ፅ/ቤት ሸልኮ የወጣው መረጃ እንደገለጸው፤ ኣቶ ኣብርሃ ብርሃነ የተባለው የድርጅቱ ሃላፊ ለስራ ማስክጃ ተብሎ የተመደበ ሁለት ነጥብ ሰዎስት ሚልዮን ብር ይዞት እንደጠፋና እስካሁን ድረስ ወንጀለኛውን ለመያዝ የተደረገው ጥረት እንደሌለ የገለጸው መረጃው፤ የዚሁ ምክንያትም በፅ/ቤቱ ውስጥ ያሉ ባለ ስልጣኖች በተጠፋፋው ገንዘብ እጃቸው ስላለበት መሆኑንና፤ ወንጀለኛው ከተያዘም እነሱን የሚነካካቸው መሆኑን ስለሚያውቁ መሆኑን ሊታወቅ ተችለዋል፣
   
    እንደመረጃው እገላለፅ እነዚህ የኣቶ ኣብርሃ ብርሃኔ ጋሻግሬዎች የሆኑ የበላይ ባለ ስልጣኖች ወደ ወንጀለኛው ስልክ እየደወሉ ከኣካባቢው ርቆ መሰወር እንዳለበት የምክር ልገሳ እያረጉለት መሆናቸውና መጀመርያውም ወደዚህ ተግባር ለመግባት የገፋፋው ምክንያት የበላይ ባለ ስልጣኖቹ የሚዘርፉት በሚልዮን የሚገመት ያገር ሃብት ኣይቶ እንደሆነ ኣንዳንድ የስራ ባለድርቦቹ ከሰጡት ሃሳብ ለመረዳት ተችለዋል፣

    ከዚሁ ከተማ ሳንወጣ ወ/ሮ ሜላት የተባሉ ነፍሰ ፁር እናት መቀሌ ከተማ ውስጥ ወደሚገኘው ኣይደር ሆስፒታል በታህሳስ 16/2006 ኣ/ም ይዛው ያለችው ህፃን ለመገላገል ብላ እንደገባች በሃኪሞቹ ሃላፊነት የጎደለውና የሞያ ብቃት ማነስ ምክንያት ሂወትዋ እንዳለፈች ያገኘነው መረጃ ኣስታወቀ፣

    የምስኪንዋ ወገናችን ቤተሰብ በዚሁ ኣስነዋሪ ድርጊት ምክንያት ክፍኛ እንዳዘኑና ሁኔታውን ኣስመልክተው ማንን ጠይቀው መልስ ሊያገኙ እንደሚችሉ ተቸግረው እንዳሉም ከቦታው የደረሰን መረጃ ኣክሎ ኣስረድተዋል፣