በመረጃው
መሰረት በታህታይ ኣድያዎ ወረዳ የሚገኙ የስርኣቱ ባለ ስልጣኖች ለመሰረተ ልማት ማስፈፀምያ ተብሎ ከመንግስት የተመደበው ከ 3 ሚልዮን ብር በላይ እንደተጠፋፋና፤ በመጠፋፋቱ ተግባርም የወረዳዋ
ኣስተዳዳሪ የነበሩ ኣቶ ኣብርሃለይ የተባለው ግለ ሰብና የስራ ኣጋሮቹ መሆናቸው ሊታወቅ ተችለዋል፣
መረጃው
ጨምሮ ገንዘቡ በመጠፋፋቱ ምክንያት የወረዳው የስራ እቅድ እንደተስተጓጎለ ኣዲስ የወርዳዋ እስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው ኣቶ ብሩህ ዘፈሩ መግለፁና፤ ስራየ ልጀምር ከተፈለገ በነ ኣቶ
ኣብርሃለይና ሌሎች ግብረኣበሮቹ የተጠፋፋው ገንዘብ ኣስቸኳይ የማጣራት ስራና ውሳኔ መሰጠት ኣለበት ብሎ እንደገለፀ ያገኘነው
መረጃ ኣስታውቀዋል፣
በመጨረሻም ይሀው ኣዲስ የከተማዋ ኣስተዳዳሪ። በዚሁ በተበላሸው የቆየ ቅጥ
ያጣው ኣሰራርና ያስተዳደር ሁኔታ ገብቶ ለመስራት ተቸግሮ ኣንዳለና ወደ ተጠያቂነት ከመግባቱ በፊት ኣስቸኳይ መፍትሄ
ይደረግልኝ ሲል በታህሳስ 20/2006 ኣ/ም ወደ ሚመለከታቸው የክልልና የዞን ባለ ስልጣኖች ኣቤቱታ ቢያቀርቡም በተጠፋፋው
ገንዘብ ውስጥ እጃቸው ስላለበት ኣወንታዊ የሆነ መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ መረጃው ጨምሮ ኣስታውቀዋል፣