Pages

Tuesday, November 20, 2012

በአፋር ክልል ሎግያ ከተማ አብሃና በተባለ ሆቴል ውስጥ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት አዛዦች ዝግ ስብሰባ እያካሄዱ መሆናቸው ታውቋል፣


    እነዚህ በሎግያ ከተማ ስቪል ልብስ ለብሰው ዝግ ስብሰባ እያካሄዱ ያሉ ከፍተኛ አዛዦች በአከባቢው እያጋጠማቸው ያለውን የህዝብና በትጥቅ ትግል በመታገል ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተቃውሞና አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል ፣
      በዚህ መሰረት በሎግያ ከተማ በከፍተኛ አዛዦች እየተካሄደ ያለው ስብሰባ በመሰረቱ የሃገርንና የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ሳይሆን የስርአቱን የስልጣን እድሜ ለማራዘም ፤ ህዝቡን አፍኖ ለመያዝና በህዝቡ የሚነሱትን ማናቸውንም ተቃውሞ ለመጨፍለቅ የሚያስችሉ ስልቶችን ከወዲሁ ለመደፍ ቢሆንም የአንድን ህዝብን ትግል በሃይል ማቆም ስልማይቻል ከልክ ያለፈ በጀት ወጪ በማድረግ እተካሄደ ያለው ገና ከጅምሩ የከሸፈ ስብሰባ የተሰብሳቢዎችን ኪስ ከማደለብ ያለፈ ምንም ዓይነት ፋይዳ እንደማይኖረው ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣