Pages

Tuesday, November 20, 2012

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በዋልድባ ገዳም አከባቢ ለስኳር ልማት ፕሮጀክት የሚያገለግል ግድብ ለመስራት ኮንትራት የወሰደው ካምፓኒ ስራውን አቋርጦ አከባቢውን መልቀቅ መጀመሩን ታውቋል፣



    በኢህአደግ መንግስት በሃገር ደረጃ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም ከተያዙት በርካታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በዋልድባ አከባቢ ሊገነባ የታሰበ ሲሆን በዚሁ ስፍራ ግድብ ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሮ የነብረው ካምፓኒ ስርዓቱ በሚከተለው ብልሹ አሰራር ምክንያት የዋልድባን ግድብ ለማሰራት የተመደበውን በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የኮርፖረሽኑ ባለስልጣናትና ሌሎች በየደረጃው ያሉ ካድሬዎችና ሽሞኞች ስላባከኑት በተከሰተው የበጀት እጥረት ችግር ምክንያት ስራውን አቋርጦ ንብረቱን ከስፍራው እያስውወጣ መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ፣
ይህ በእንዲህ እያለ በዋልድባ ገዳም አከባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ደን የተሸፈነ ቦታ ነባር የህወሓት ታጋዮች መንጥረው ከሰል በማሰል እንዲጠቀሙበት እንደተሰጣቸው ከአከባቢው የአረሰን ዘገባ ያመለክታል ፣
   በማህበር የተደራጁት ነባር ታጋዮች ከጀርመን ሃገር ባስገቡት ማሽን እየተጠቀሙ ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን የተፈጥሮ ደን እያወደሙት በመሆኑ የአከባቢው ህዝብ እያማረረ መሆኑ ታውቋል ፣
    በማክሰል ስራ የተሰማሩ ነባር ታጋዮች ያከሰሉትን ከሰል በፈለጉት ቦታ በመሄድ በ 280 ብር ሂሳብ እንዲሸጡ በስርዓቱ የተፈቀደላቸው ሲሆን ከአንድ ጆንያ ከሰል ሽያጭ ብር 25 እየተቆረጠ ገቢነቱ ለማን መሆኑ የማይታወቅ ገንዘብ እየተሰበሰበ መሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ያስረዳሉ ፣ የኢህአደግ መንግስት ፋብሪካውን በዚሁ ስፍራ ለመትከል በጀመረበት ወቅት ከፍተኛ ተቓውሞ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳጋጠመው የሚታወቅ ነው፣