Pages

Tuesday, November 20, 2012

በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን በታሕታይ አድያቦ ወረዳ በሸራሮ ከተማ በዋና አስተዳደሪው አቶ ጥላሁን በርሀ የሚመራው የግብር አሰባሰብ በተመልከተ የሚካሄደው ሰብሰባ በህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደ ገጠመው ተነገረ፣



       ህዝቡ በሸራሮ ከተማ በዕለት 08/03/2005ዓ/ም በአቶ ጥላሁን በርሀ የቀረበው አግባብነት የሌለውን የግብር አከፋፈል በተመለከተ የሚካየደውን ፍፁም እንደማይቀበለውና በዚህ ምክንያት ዳግም በመላ ሃገራችን ተስፋፍቶ የሚታየው የገበያ ውድነትና የአቅርቦት መጥፋት በወረዳችን በሰፊው እያጋጠመ ስለ ሆነ ነዋሪው ህዝብ ልንከፍል ፍቃድኛ አይደለንም እንዳሉ ታውቋል፣
ከእነዚህም ፍትሃውነት የጎደሎው ከአቅማቸው በላይ እያንዳንዳቸው 53,000ብር እንዲከፍሉ ከታዘዙት ወገኖች መካከል።-
1.አታክልቲ የተባለ የወጋሕታ ምግብ ቤት ባለቤት
2.ጎይቶኦም ማርቆስ
3.ሽራተን ምግብ ቤት በሚል በሸራሮ ከተማ የሚገኝ ሲሆኑ ወዲ ሴሮ የተባለ ነጋዴ ደግሞ ከ100,000 ብር በላይ ሊከፍል እንደተወሰነበት ታውቋል፣
    ይህንን መቋቋም የማይችሉትን በዚሁ አስተዳደር በአቶ ጥላሁን በርሀ በተመራው ስብሰባ የተገኙ ነዋሪዎችና ሌሎች ወገኖች የኢህአዴግ ስርዓት እየተከተለው ያለውን ህዝባውነት የጎደለው አስተዳደር አመራርና የግብር አወሳሰን የከተማ ሽፍቶች በሚል የተቃውሞ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ እያሰማ መሆኑ ታውቋል፣
ከአሁን በፊትም በመቀሌና በወረታ ያለውን የኑሮ ሁኔታ በተመለከተ የገለፅን መሆናችን ይታወሳል፣