Pages

Saturday, May 18, 2013

በትግራይ ማእከላዊ ዞን ፤ በታሕታይ ማይጨው ወረዳ የሚገኙ በግብርና የሚተዳደሩ ገበሬዎች ማዳበሪያ አንወስድም በማለታቸው ምክንያት ከመንግስት ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎት እንዲታገዱ መደረጉን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደርሰን ዘገባ መሰረት አሁን ባለው ውድ ዋጋ ማዳበሪያን ገዝቶ መጠቀም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ገበሬውን ለዕዳ ይዳርጋል  በመሆኑም የመንግስት ሽሞኞችን ለማስደሰት በሚል ተገፋፍተን ማዳበሪያ አንገዛም አስፈላጊ ከሆነም አምና የገዛነው ስላለ እሱን መጠቀም እንችላለን በማለት አርሶ አደሮቹ መቃወማቸውን ቷውቋል፣
የገብሬዎቹን ተቃውሞ ተከትሎ አርሶ አደሩ ማዳበሪያ እንዳይገዛ አነሳስታችሃል በሚል አቶ በርሀ ተስፋሁነይና አቶ ተኸለ አስፍሃ የተባሉ የአከባቢው ኗሪዎች በመንግስት የሚሰጠውን አገግሎት እንዳያገኙ መታገዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
በተመሳሳይ በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የተሰበሰቡት የስድስት ወረዳ የህወሓት አባላት ማዳበሪያ አንወስድም ማለታቸው ቷውቋል ፣
      ማዳበሪያ አንወስድም ያሉት የድርጅቱ አባላትን ለማግባባት የሚመለከታቸው የዞኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቦታው በመገኘት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስብሰባ ቢያካሂዱም የሚቀበላቸው ስላላገኙ ማንኛውም አርሶ አደር መንግስት የሚለውን መተግበር ስላለበት የእርሻ መሬት የያዘ ሁሉ ማዳበሪያ የግድ መውሰድ አለበት ፥ የሚያንገራግር ካለም የእርሻ መሬቱ ከመነጠቁ በተጨማሪ ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ ይደረጋል በሚል መመሪያ  ስብሰባውን አጠቃለውታል ፣