በሰ/ምዕራብ ትግራይ ፤ በመደባይ ዛና ወረዳ ፤ የሰለክላካ ከተማና አከባቢዋ ኗሪ ህዝብ በከተማዋ የሚታየውን
የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንዲቃለልለት ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ያቀረበውን ስሞታ ቱክረት አግኝቶ ሊፈታለት ስላልቻለ
ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መገደዱን ቷውቋል፣
ህዝቡ በሰላማዊ ሰልፍ ካነሳቸው ጥያቄዎች መካከል ለከተማዋ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተብሎ ተመደበ የተባለው
በጀት የት ገባ ? የተመደበውን በጀት የዘረፉ ሽሞኞች ለፍርድ ይቅረቡ? የሚሉ ይገኙበታል፣
ይህ በእንዲህ
እያለ ሚያዝያ 16/2005 ዓ/ም ከሰለኽለኻ ከተማ ወደ ሽረ እንዳስላሰ በመጓዝ ላይ የነበረና በአከባቢው በሚገኘው የተበላሸ የመኪና
መንገድ ምክንያት የመገልበጥ አደጋ የደረሰበት አንድ የህዝብ ማማላለሻ አውቶብስ ውስጥ ተሳፍረው ከነበሩት መገደኞች መካከል በዘጡኙ
ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶ በሽረ እንዳስላሰ በሚገኘው ስሑል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣