በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ ጃዊ ወረዳ የሚኖሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ገበሬዎች ለብዙ ዓመታት በህጋዊ መንገድ
ተረክበው ሲጠቀሙበት የቆዩ የእርሻ መሬት በኢህአዴግ ስርዓት የቀረበውን ማዳበሪያ በተጠየቁት ዋጋ እንዲገዙ ፤ ካልሆነ የእርሻ መሬታቸውን
በመቀማት ማዳበሪያ ለመግዛት ፈቃደኛ ለሆኑ ግለሰቦች ይሰጣል የሚል በመመሪያ መልክ እንደተነገራቸው የአከባቢው አርሶ አደሮች ይናገራሉ፣
የአከባቢው የመስተዳድር አካላት ሃላፊነታቸውን አለአግባብ በመጠቀምና አርሶ አደሩን በማስፈራራት ሳያስፈልገው
ማዳበሪያ ገዝቶ አላስፈላጊ ዕዳ ውስጥ እንዲዘፈቅ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አርሶ አደሩ አስቀድሞ ስለተገነዘበው ማዳበሪያን እንዲገዛ
ለመገፋፋት የተካሄደው ተደጋጋሚ ስብሰባ ስኬታማ ሊሆን እንዳልቻለ ቷውቋል፣
በሁኔታው ቅር የተሰኙ የአከባቢው የመስተዳድር አካላት መሬት የመንግስት እንጂ የግለሰብ ስላልሆነ የመንግስት
መመሪያን የማይቀበል አርሶ አደር ካለ የእርሻ መሬቱን በመንጠቅ አስተዳደሩ ለሚፈልገው ሰው እንዲሰጥ ይደረግ የሚል መመሪያ ከዞኑ
ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባዘዘው ጫኔ ስለወረደና የአከባቢው ገበሬዎችም የማዳበሪያ ዋጋ መወደድን አስመልክተው በተደጋጋሚ ያቀረቡትን
ስሞታ ሰሚ ስላጣ አርሶ አደሩ መንግስት በተዘዋዋሪ ካቋቋማቸው የንግድ ተቋማት ሳይወድ የግድ ተበድሮ ማዳበሪያ በመግዛት በማይወጣው
ዕዳ ውስጥ እየገባ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፣
በሌላ በኩል የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩና በህጋዊ መንግድ ከጦሩ ተሰናብተው በሌላ ስራ ተሰማርተው
ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ዜጎችን መንግስት ምክንያት እየፈጠረ እያሰራቸው መሆኑን ቷውቋል፣
እነዚህ
ከጦሩ ተሰናብተው በተለያየ ስራ በመሰማራት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ሲንቀሳቀሱ ተይዘው ያለምንም ወንጀል በፍኖተ ሰላም
ከተማ በሚገኘው እስር ቤት ከታሰሩት በርካታ ስማቸው ያልተገለጸ ነባር የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ኗሪነቱ በቡሬ ከተማ የሆነ
፳/አለቃ አስረስ ድጉማ እንደሚገኝበት ለማወቅ ተችሏል፣