Pages

Sunday, January 19, 2014

የህወሃት ኢህኣዴግ ባለስልጣኖች በመጪው ዓመት ለሚያካሂዱት ኣገራዊ ምርጫ ኣስመልክተው ስብሰባዎች በማካሄድ ስራ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለፀ፣




በተገኘው መረጃ መሰረት በሁሉም የትግራይ ኣካባቢዎች የሚገኙ ዘኖች፤ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በየደረጃው ተከታታይ ስብሰባዎች በማካሄድ ላይ የሚገኙ የህወሃት ኢህኣዴግ ባለ-ስልጣኖች እንደ ዋና የመሰብሰብያ ኣርእስት ሆኖ እየቀረበ ያለው ኣጀንዳ በቀጣዩ የ2007 ኣ/ም ኣገራዊ ምርጫ ገዢው ፓርቲ የኢህኣዴግ መንግስት እንዴት ማሸነፍ እንዳለበትና እያንዳንዱ የስርኣቱ ኣባልና ካድሬ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በምርጫው ወቅት የተለመደው የማጭበርበር ስራ እንዲያከናውንበት በሚያስችል ትምህርት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፣
      በተለይ ቀደም ብለው ተጥለውና ተረስተው የነበሩት ነባር ታጋዮች፤ ካድሬዎችና የህወሃት ኣባላት እንደገና ኣታልለው የስልጣናቸው ማራዘምያ ኣድርገው ሊጠቀሙባቸው ስለፈለጉ የህዝቡ ተቀባይነት ኣላቸው ብለው እምነት ለጣሉባቸው ግለሰቦች በስብሰባው ላይ በማሰማራት ከጥር 3/ 2006 ኣ/ም ጀምረው መጠነ ሰፊ የሆነ እንቅስቃሴ እያካሄዱ መሆናቸው ተገለፀ፣
      እነዚህ በህወሃት ኢህኣዴግ ስርኣት ደማቸው ያፈሰሱትና የወጣትነት ግዜያቸው በከንቱ ያለፈው ለኣመታት ተበድለው የቆዩ ተሰብሳቢዎች ስርኣቱ ምን ያህል የማደናገር ችሎታ እንዳለው በሚገባ ስለሚያውቁ፤ የስርኣቱ ካድሬዎች በከፈቱት የስብሰባ መድረክ ላይ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ለማጥላላትና ለማግለል ቢሞኩርም ለቀረበው ተራ ኣነጋገር እንዳልተቀበሉት መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣
      በመጨረሻ! የስብሰባው መሪዎች ኣረናና ቅንጅት ጸረ ህዝቦችና ሰው መሳይ ተናዳፊ እባቦች በመሆናቸው ህዝቡ ሁኔታቸው ሳያውቅ እንዳይመርጣቸው ኣስተምርዋቸው ብለው በተናገሩበት ሰኣት ተሰብሳቢዎቹ ማነው ፀረ ህዝብና የህዝቡን ኣደራ የረሳው በሚገባ ተዋውቀናል በዛን ቀን እንገናኝ ሲሉ በድፍረት ሃሳባቸው እንደገለፁ ለመረዳት ተችለዋል፣