Pages

Saturday, January 25, 2014

የትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ኣስተዳዳሪዎች ከባለ-ሃብቶች ግቦ እየተቀበሉ ህጋዉነት ባልተከተለ መንገድ መሬት እየሸጡ መሆናቸው ታወቀ፣




በምዕራባዊ ዞን ኣያስተዳደሩ የሚገኙ የስርኣቱ ሽማምንቶች የሆኑት። ኣቶ ፍሰሃ በርሀ ዋና ኣስተዳዳሪ፤ ኣቶ ሃፍቱ ምክትል ዋና ኣስተዳዳሪና ኣቶ ግርማይ ዘርኡ የገጠር እርሻ ልማት ሃላፊ በመሆን በዞኑ የሚገኝ ሰፊ ለም መሬት ግቦ ለስጥዋቸው ባለ ሃብቶች ህግና ኣሰራር በጣሰ መንገድ መሬት እንዲወስዱ እያደረጉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል፣
    እነዚህ ባላቸው ስልጣን ተጠቅመው የማይገባቸው ግላዊ ጥቅም በማካበት ላይ የሚገኙ ኣስተዳዳሪዎች የሆነ ሰው ከሁለት ኣመት በላይ ቀዋሚ ነዋሪ ሆኖ በዞኑ ካልቆየ መሬት ኣይሰጠዉም የሚል የመሬት ኣስተዳደር ደምብ ቢኖርም። ሁለት ኣመት ላልተቀመጡ 11 ባለሃብቶች ከየኣንዳንዳቸው መቶ ሺ የሚደርስ ግቦ በመቀበል ከተቀመጠው ኣሰራር ውጭ መሬት እንዲሰጣቸው የሚፈቅድ ትእዛዝ በመስጠታቸው ምክንያት በኣከባቢው ነዋሪዎች ተቃዉሞ ኣስነስቶ ኣስቸካይ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለፀ፣
     መረጃው ጨምሮ እንዳስርዳው የዞኑ ምክርቤት የኣስራ-ኣንዱ ሰዎች የመሬት ድልድል ኣስመልክቶ ባካሄደው ስብሰባ ሁለት ኣመት በዞኑ ያለሞኖራቸው ብቻ ሳይሆን በኮንትሮባንድ ንግድ ተሰማርተው የቆዩ ሰዎች ሞሆናቸው እየታወቀ ለምን መሬት ተሰጣቸው የሚል ክርከር እንዳስነሳ ያስረዳው መረጃው ከኣስረኣንዱ ሰዎች ወዲ ሽረ የተባለው ግለ ሰብ መሬት ሊያገኙ የቻሉት ለያንዳዱ ኣስተዳዳሪዎቹ  መቶ ሺ ብር ግቦ ስለ ሰጡ ነው ብሎ በማጋለጡና ሚስጥራዊው መረጃው ወደ ምክርቤቱ በመድረሱ ምክንያት መግባባት ላይ እንዳልቻሉ መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣
    በተመሳሳይ መንገድ የሸራሮ ከተማ ዋና ኣስተዳዳሪ ታደሰ/ወዲ ኣወጣሽ/ ፍትሓዊ ኣሰራር ኣጥፍቶ ብልሹ ኣሰራር እንዲነግስ እያደረገ  በመሆኑ። የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ከሃላፍነቱ ይዉረድልን በማለት በተከታታይ ጥያቄና ተቃዉሞ በማሰማት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል፣