Pages

Saturday, January 25, 2014

በትግራይ ክልል ለኮንዶሚኒየም ቤቶች መስርያ ተብሎ የተመደበ ገንዘብ በክልሉ ባለስልጣናት በመበላቱ ምክንያት የቤቶቹ ግንባታ ተቋርጦ እንደሚገኝ ተገለፀ፣




በመረጃው መሰርት በትግራይ ክልል የቤቶች ግንባታ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ሳህለ ገብረስላሴ ለኮንዶሚንየም ቤቶች መገንቢያ ተብሎ  የተመደበ ገንዘብ በመጨረሱና፤ ለነዚህ በገንዘብ ምክንያት ግንባታቸው የተቋረጡ የኮንደሚንየም ቤቶች እራሱ ግንባታቸውን ጨርሶ ለሚጠቀም ሰው ልንሽጣቸው ነው ብሎ ባስታወቀበት ግዜ ህዝቡ በበኩሉ ለነዚህ ቤቶች ግንባታ  የተመደበውን ገንዘብ ባለስልጣናት ለግል ጥቅማቸው ስላዋሉት እንጂ፤ ለቤቶቹ ግንባታ በቂ ገንዘብ እንደተመደበ በሚዲያዎችና በተለያዩ የውይይት መድረኮች ተንግርዋል በማለት ተቃውሞአችውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀዋል፣
    መረጃው ጨምሮ ህዝቡ ተቃውሞውን እያሰማባቸው ካሉ ሓሳቦች መካከል መንግስት የጀመራቸው የኮንዶሚኒየም የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት አቅም ለሌላቸው ዜጎች እንደሆነ ሲገልፅ ቆይቶ፥ ኣሁን ታድያ ለምን በህዝብ ስም ሲሰሩ የቆዩ ቤቶችን ገንዘብ አጥሮናል በሚል ምክንያት፤ ሃብት ላላቸው ሰዎች ልንሽጣቸው ነው እያለ ያለው? ለነዚህ ቤቶች ግንባታ ተብሎ የተመደበ ገንዘብስ የት ገባ? ይህ ገንዘብ የት እንደገባ ገለልተኛ በሆነ አካል ተጣርቶ ለህዝቡ መነገር አለበት? የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች አንስተው እንደተቃወሙ ተገልፅዋል፣
      በመጨረሻም ህዝቡ በመሰራት ላይ የነበሩ ግን ደግሞ ግንባታቸው ሊጥናቅቅ ከተቃረቡ በኋላ በገንዘብ እጥረት አመካኝተው ግንባታቸውን እንዲቆም ያደረጉ የፕሮጀክቱ ባለ ስልጣናት ገንዘብ ላላቸው ወዳጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ሽጠው ከልክ ያለፈ ትርፍ ገንዘብ ለማግኘት የሚያካሄዱት መላ ነው ካሉ በኋላ። እነዚህ ቤቶች ቢሽጡም እንኳን በግልፅ ህዝቡን አሳታፊ በሆነ መንገድ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፣