Thursday, January 30, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች በሙስና ተግባር ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለፀ፣




የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፤ ምክትሉና የዞኑ ግብርና  ሃላፊ በሕብረት ከ300 ሺ በላይ ግቦ እንደተቀበሉ ከህዝብ በተገኘው መረጃ ከታወቀ በኋላ ጉቦ ወስዳቹሃል ሲባሉ ሊያምኑ ስላልቻሉ፤ የዞኑ ካብኔ በከባድ ንትርክና መሳሳብ ተጠምደው ከሰነበቱ በኋላ፤  በአሁኑ ግዜ ማመናቸው  ከሁመራ ከተማ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
    እነዚህ በሙሱና የተጨማለቁ የዞኑ አሰተዳዳሪዎች ቆይተው ጉቦ እንደተቀበሉ ለማመን የቻሉት ከሁለት ሳምንት በላይ ካደረጉት ግምገማ በሃኋ መሆኑ የገለፀው መረጃው በጉቦ መልክ የተቀበሉት 300 ሺ ብር እስካሁን በህዝብ ትብብር ያመኑበት እንጂ ከዚህ በላይ ጉቦ ተቀብለዋል የሚል እምነት በሁመራ ከተማ ነዋሪ ህዝብ መቅረቡና ጉቦ በተቀበሉት አስተዳዳሪዎች የተወሰደ ቅጣት ባለ መኖሩ ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ህግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ ህዝቡ እየጠየቀ እንደሚገኝ አስረድተዋል፣
    ጉቦ የመቀበል ተግባር ከላይ እስከ ታች ያሉ የስርዓቱ አስተዳዳርሪዎች የተለመደ ተግባራቸው በመሆኑ፤ ራስ በራሳቸው አሳልፍው እንዳይሰጣጡ ካላይ’ና ከታች እየተደጋገፉ ባሉበት ሁኔታ፤ አሁንም ጥፋታቸውን ለመሸፈን ሲሉ የተለያየ ምክንያት እያቀረቡና ለዚሁ አስነዋሪ ድርጊት ለሚፈፅሙትም አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዳይወሰድባቸውም መሰናክል እየፈጠሩ ናቸው ሲሉ በርከት ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ሃሳባቸውን እየገለፁ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል፣