ከስፍራው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በስልጣን ላይ ያለው የኢህ.አ.ዴ.ግ
ቡድን በኦሮሚያ ክልል የተለየዩ ሰበቦችን እየፈጠረ የገደላቸውንና አስሮ እያሰቃያቸው የሚገኙትን ንፁሃን ዜጎች በተመለከተ እያጋጠመው
ያለውን ተቃውሞና የፖለቲካ ኪሳራ ለመሸፈን ሲል ታማኝ ካድሬዎችን አሰማርቶ የኦሮሚያ ህዝብ ባለፉት ስርዓቶች በተለይ በሚኒልክ ዘመነ መንግስት እየታረዱ ይገደሉ እንደነበርና በኢ.ህ,አ,ዴግ ግን ዲሞክራሲያዊ
መብቱ የተረጋገጠ ለማስመሰል ላይና ታች እያለ እንደሚገኝ ታውቋል፣
ለቅስቀሳ ተብለው
እየተወቀሱ ያሉት ያለፉት የደርግና የሃይለስላሴ ስርዓቶች፤ የኦሮሚያን
ህዝብ ያስሩትና ይገድሉት ስለነበር በዚህ ምክንያትም ተረግጦና ተጨቁኖ እንደነበር፤ ዛሬ ግን በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ዘመነ መንግስት ክብሩና
ዲሞክራሲያዊ መብቱ እንደተጠበቀለት ለማስመሰል ያለመ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል፣
ይህ በእንዲህ
እንዳለ በስልጣን ላይ የሚገኘው የአምባገነኖች ስርዓት በአለፉት ስርዓቶች ተፈፀመ ከሚለው ግፍ በባሰ መልኩ እራሱ እየቀጠለበት ሲሆን፤
በተለይ ለህዝብ በዚህ ዘመን ሰለ-ሚኒልክ ቅስቀሳ በማካሄድ በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል የጥላቻ ቁርሾ እንዲፈጠር በማድረግ መተማመንን
በማጥፋት የስልጣን እድሜውን ለማራዘም እያደረገ ያለው እኩይ ተግባር አነጋጋሪ ጉዳይ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣