በትግራይ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው
በሰራዊቱ መካከል አጋጥሞ ላለው የመበታተንና የመጥፋት ሂደት፤ ከአራትና ከአምስት አመታት በፊት ከመከላከያ ሰራዊት ወጥተው የግል
ኑሮአቸውን ሲመሩ ለነበሩ ወታደሮች ከየአካባቢው በማደን የጎደለባቸውን ቦታ ለመሙላት ላይና ታች በማለት ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ
ለማወቅ ትችሏል፣
ከውትድርናው አለም ተሰናብተው በሲቪላዊ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው የቆዩትን ዜጎቻችን የወያኔ
ኢህአዴግ ስርዓት ከመከላከያ ሰራዊት ከተሰናበቱበት ሰዓት እስካሁን
ድረስ የት ወድቃችኋል ብሎ አስታወሷቸው እንደማያውቅ የገለፀው መረጃው፥
በአሁኑ ጊዜ ግን ክፍተቱን ለመሙላትና ሊጠቀምባቸው ስለፈለገ፤ በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተቃውሞ እያጋጠመው እንደሚገኝ ከምንጮቻችን
ያገኘነው መረጃ አስረድቷል፣
በተመሳሳይ
በሁሉም ግንባሮች የሚገኙ የኢህአዴግ ጉጅሌ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከፋ መልኩ ሰራዊቱን እየተው ወደ ቤተሰቦቻቸውና ወደ ጎረቤት
ሃገሮች በመጥፋት ላይ እንዳሉ የገለፀው መረጃው፤ መነሻውም ስርዓቱ በላያቸው ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ጥሰትና ኢ-ዴሞክራሲያዊ
አካሄድ እንደሆነ ከመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፣
በሰራዊቱ መጥፋት የተቸገሩ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ከሰራዊቱ በመጥፋት
ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሄዱ የሰራዊት አባላት ይዞ ወደ ሰራዊቱ ለመመለስ ለስርዓቱ ታማኝ የሆኑ ካድሬዎችንና ተላላኪዎችን በየአካባቢው
በማሰማራት ከአስተዳድሮች እና ከፀጥታ አካሎች ጋር በመመሻጠር አስረው እንዲመልሱላቸው ትዕዛዝ እንዳስተላለፉ ለማወቅ ተችሏል፣