የህወሃት ኢህአዴግ ገዢው
መንግስት ግንቦት 2007 ዓ/ም አስመሳይ ምርጫ ለማካሄድ እየተንቀሳቀሰ
ባለበት በአሁኑ ግዜ፤ የትግራይ ህዝብ ሊመርጠው እንደማይችል አስቀድሞ በማወቁ፤ ስልጣኑን ላለመልቀቅና የህዝቡን ድምፅ ሰርቆ አሸነፍኩ
ለማለት፤ በከተማና በገጠር ለሚነሳ ተቃውሞ በሃይል ጨፍልቆ ለማበርከክ በክልል ብቻ የሚመሩ የአድማ በታኝ ፖሊስ ሃይል፤ ከጥቅምት
20 ጀምሮ እያሰለጠነ መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቁ፣
የአድማ በታኝ ፖሊስ ሃይል እስከ አሁን ድረስ ከፌደራል ውጭ ስልጠና ተሰጥቶ
እንደማይታወቅ የገለፀው መረጃው፤ የትግራይ ክልል አስተዳደር ግን የህወሃት ማሌሊት ህልውናን ለማስቀጠል ሲል፤ ከተለያዩ ወረዳዎች
የተውጣጡ በርከት ያሉ ሰልጣኞች እያሰለጠነ መሆኑንና፤ በማንኛውም ባለስልጣን የተሰጣቸውን ትእዛዝ ያለተቃውሞ እንዲፈፅሙ የተዘጋጁ
እንደሆኑም መረጃው አክሎ አስረድቷል፣