ለተከታታይ
ቀናት በህወሓት-ማሌሊት ካድሬዎች ሲካሄድ በሰነበተው ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢ የመንግስት ሰራተኞች ካነሷቸው ሃሳቦች ለመጥቀስ ያህል
መልካም አስተዳደር የሚባል የለም፤ ፍትህ ጠቅልሎ ጠፍቷል፤ ህወሓት- ኢህአደግ እየተከተለው ባለው ብልሹ አስራር ህዝባችን በችግር
ላይ ወድቆ ይገኛል የሚሉና ሌሎችም እንደነበሩ ታውቋል።
በስብሰባው ላይ ሃይለኛ የተቃውሞ ሃሳቦች ያቀረቡ ሰዎችን ለመጥቀስ በአድዋ
የሚገኘው የዩኒቨርሲቲ ምክትል ሃላፊ አቶ ካሕሳይ ደስታ፤ የዩኒቨርሲቲው
ፀሃፊ ይግዛው በየነና ሌሎች ሲሆኑ ህዝባችን በከፋ የኑሮ ሁኔታ እያለ የስርዓቱ ባለስልጣናት ግን በክራይ ሰብሳቢነት በልፅገዋል
ብለው ሃሳባቸውን ስለገለፁ ብቻ ወድያውኑ ታስረው እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።