Pages

Saturday, November 29, 2014

የአብይ ዓዲ ከተማ ነዋሪዎች የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው በኢህአዴግ ካድሬዎች እየታደኑ በመታሰር ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በከተማዋ የአቶ ስየ አብረሃ መልእክትና የዓረና የመድረክ ድርጅት ወረቀቶች ተበትነው እንደነበሩ መረጃው ገልፆ ይህንን ምክንያት በማድረግ የስርዓቱ ካድሬዎች የጠረጠሯቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች በማስፈራራት እያሰሯቸው እንዳሉና  ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሰው  ማህበራዊ ህይወታቸውን እንዳይመሩ እንቅፋት ሁነውባቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ አመለከተ።
   መረጃው በማስከተል- በስርዓቱ ካድሬዎች ከታሰሩት መካከል አቶ ካሕሳይ የተባለ ወገን ሲሆን ይህ ዜጋ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ ዕለታዊ ኑሮውን የሚመራ ሰላማዊ ሰው እንደሆነና ተኝቶ ከነበረበት አሉላ ሆቴል አስወጥተው አንተ ፀጉረ ለውጥ ነህ በሚል ምክንያት  አስረው እንደወሰዱት ለማወቅ ተችሏል።
      እንደ ሚታወቀው በአብይ ዓዲ ከተማ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች በከተማዋ የተበተነውን ወረቀት በእናንተ አማካኝነት ነው የተበተነ ተብለው በስርዓቱ ካድሬዎች እየታሰሩ እንደሰነበቱ ከዚህ በፊት በዜና እወጃችን የገለፅን ሲሆን አሁንም  የሃይማኖት አባቶችን የማሰር እኩይ ተግባር ስርዓቱ አጠናክሮ እየቀጠለበት እንደሚገኝ ከከተማዋ የሚገኙት ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል።