Pages

Wednesday, November 26, 2014

በአብይ ዓዲ ከተማ የሚኖሩ የሃይማኖት መሪዎች የአረና ትግራይ ድርጅት ተባባሪዎች ናችሁ እየተባሉ በፖሊሶች እየታደኑ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከከተማው አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ማእከላዊ ዞን በአብይ አዲ ከተማ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች ከተቃዋሚ ድርጅቶች በተለይ ደግሞ ከዓረና ትግራይ ድርጅት ጋር ትተባበራላችሁ በሚል ምክንያት ቄሶቹን እንዲታሰሩ ከክልል በወረደው መመርያ መሰረት ፖሊሶች በቁጥጥር ላይ ለሟዋል በከተማዋ ተሰማርተው እንደሚገኙ ተገለጸ።
     መረጃው ጨምሮ ባለፈው ሳምንት በአብይ ዓዲ ከተማ የአረና ትግራይ ድርጅትን ዝርዝር አላማ የያዙ በርካታ ፓምፕሌቶች እንደተበተኑ በመግለፅ የተበተነው ፅሁፍም በከተማዋ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች ከአረና ድርጅት አባላት ጋር በመተባበር ነው የበተኑት በማለት የስርአቱ ካድሬዎች ነዋሪውን ሰብስበው እንደተናገሩት ለማወቅ ተችሏል።