Pages

Wednesday, December 3, 2014

በማንኩሳና ፍኖተ ሰላም ከተማ ውስጥ “ወደ ከተማችን አሸባሪዎች ገብተዋል በማለት” የስርአቱ የጸጥታ አባላት ከ68 ሰዎች በላይ ማሰራቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ።



የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በምዕራብ ጎጃም ዞን በማንኩሳና ፍኖተ ስላም ከተማዎች ውስጥ ህዳር 18/2007 ዓ/ም ወደ ከተማችን አሸባሪዎች ገብተዋል በሚል ምክንያት የስርአቱ የፀጥታ ሃይሎች ምንም አይነት ወንጀል የሌላቸውን ንፁሃን ሰዎች ያሰሩ ሲሆን ከማንኩሳ ከተማ 50 ነጋዴዎች ሲታሰሩ፤ በተመሳሳይ ከፍኖተ ሰላም ከተማ ደግሞ ከ18 በላይ ነዋሪዎች  መታሰራቸው ተገልጿል።
   እነዚህ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት ንፁሃን ወገኖች ለሁለት ቀናት ያህል እየደበደቡ እንዳሰቃዩዋቸውና እነዚህ ንፁሃን ስዎች ከባድ ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላም የተወሰኑት መፈታታቸውን መረጃው የገለጸ ሲሆን በወቅቱ ከ 200 በላይ የሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት በፓትሮል መኪና እየተንቀሳቀሱ የከተማዋን የሰላም ሁኔታ ማወካቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።