በምንጮቻችን መረጃ መሰረት
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙት የተለያዩ ወረዳዎች የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በየአከባቢው እንደሚከበር የሚታወቅ ሆኖ በስልጣን
ላይ ያለው የኢህአደግ ገዢው ብዱን በአሉን በሚከበርበት ሰአት ከህዝቡ ይሁን ከተቓዋሚ ድርጅቶች ሊደርስባቸው ከሚችል ጥቃት በመስጋት
የደህንነትና የፖሊስ አባላት በማሰማራት ንፁሃን ሰዎችን በማሰርና በማንገላታት ላይ እንደሚገኝ ታወቀ።
በዚህ መሰረትም በባምባስ ወረዳ 5ት የትግራይ መታወቅያ ወረቀት የያዙ ወጣቶች
በስርአቱ የታጠቁ ሃይሎች ተኝተውበት ከነበሩ ሆሮ ከተባለው መኝታ ቤት እየድበደቡ በማስወጣት እንዳሰሩዋቸው የገለፀው መረጃው በአሶሳ
ከተማ በሚገኘው የስርአቱ ተላላኪ የሆነው ዳኛም ለነዚሁ ንፁሃን ወገኖች በሃሰት ማስወንጀሉንና በዚህም የተነሳ በአካባቢው ለአምስት
ቀን ያህል ኔት ወርክ እንዲቋረጥ መደረጉ ተገልጿል።
በመጨረሻም መረጃው እንዳመለከተው የስርአቱ ካድሬዎች ስጋት የተነሳ፣ የታሰሩት
ወጣቶችን በኤርትራ መንግስትና ግብፅ የተላኩ አሸባሪዎች ተገኙ በሚል ምክንያት በዳቡስ፤ ባምባስና ሌሎች ወረዳዎች አራት ( 4ት ) የፍተሻ ኬላዎች በማቛቛም ጥብቅ ፍተሻ እያካሄዱ መሆናቸውን
መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።