በመረጃው መሰረት በኦሮሚያ ክልል፤ ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ ስልኪ አምባ ወረዳ
ውስጥ የሚኖረውን ህዝብ ከህዳር 16/2007 ዓ/ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በተከታታይ ስብሰባ ላይ እንደሚገኝና አብዛኛው የስብሰባው
ተሳታፊ ህዝብ አርሶ አደር ከመሆኑ የተነሳ ሰብሉን በወቅቱ መሰብሰብ እንዳልቻለና በዝናብ እየተበላሸ መሆኑን የገለፀው መረጃው እየተካሄደ
ካለው ስብሰባ የቀረ ማንኛውም ሰው ደግሞ 500 ብር ይቀጣል የሚል ትእዛዝ ስለተላለፈ ሳይወድ በግድ እየተሳተፈ መሆኑ ታውቋል።
በስብሰባው ላይ የቀረበው አጀንዳ እየታየ ያለው ልማት እንዲቀጥል ከተፈለገ
በመጪው ግንቦት 2007 ዓ/ም በሚካሄደው ምርጫ ላይ ኦህዴድ ኢ.ህ.አ.ደ.ግን መምረጥ አለባችሁ የሚልና የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ መብት
የሚፃረር ትእዛዝ ተላልፎ ስለሚገኝ ተሰብሳቢው ህዝብ በፊናው ስርዓቱ በዞናችን ውስጥ ያከናወነው ልማት የለም በማለት ተቃውሟቸውን
እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል።