የኢህአዴግ ቡድን ባለስልጣኖች
በዚህ አመት የሚካሄደውን አስመሳይ ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፍትሃዊ፤ ሰላማዊ፤ ዴሞክራሲያዊና ታማኝ ይሆናል ብለው በተለያየ አጋጣሚዎች
እየገለፁ ቢሆኑም በተግባር ግን የተቃዋሚ ድርጅት አባላትና አመራሮች የቅስቀሳ ስራቸውን እንዳያሳልጡ በማሰር ተግባር ላይ መሰማራታቸውን
የደርሰን መረጃ ገልፀ።
በተለይ በጥምረት የሚንቀሳቀሱትን የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲ ተቃዋሚ
ድርጅቶች ህዳር 21/2007 ዓ/ም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ህዝባዊ
ስብሰባ ለማካሄድ ፈቃድ ጠይቀው እንደተከለከሉ የገለጸው መረጃው። የጥምረቱ ሊቀ-መንበር የሆነው ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አጠቃላይ
የሚያካሂዱትን እንቅስቃሴ የሲቪል ልብስ በለበሱ የደህንነት አባላት ጥብቅ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነና እለታዊ ስራዎቻቸውንም
በነፃ ማከናወን እንዳልቻሉ የተገኘው መረጃ አብራርቷል።
እነዚህ ጥምረት ያደረጉ ሁለት የተቃዋሚ ድርጅቶች በመተማ ወረዳና በጎንደር
አካባቢ በሚገኙት ወረዳዎች ጽሕፈት ቤት እንዳይከፍቱ፤ በራሪ ወረቀቶችን ወደ ህብረተሰቡ እናዳያሰራጩና ህዝባዊ ስብሰባ እናዳያካሂዱ
መከልከላቸውንና ይህ የማደናቀፍ ድርጊትም ገዥው ስርአት በሃገር አቀፍ ደረጃ በሰፊው እየተጠቀመበት መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።