Pages

Saturday, December 6, 2014

በደቡብ ክልል የሚገኙ ወጣቶች ወደ ውትህድርና እንዲገቡ በማለት በገዢው የኢህአዴግ ካድሬዎች እየተገደዱ መሆናቸውን ምንጮች ከአካባቢው የላክሉን መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት በደቡብ ክልል በሃዋሳ፤ ሆሳእና፤ አርባ ምንጭና ሌሎች ከተማዎች የሚገኙ ወጣቶች ወደ ውትህድርና እንዲገቡ በኢህአዴግ ስርአት ካድሬዎች እየተገደዱ ቢሆኑም፤ ወጣቶቹ ግን በመከላከያ ውስጥ ወታደሮች እየደረሰባቸው ያለውን ግፍና ሰቆቃ እያየን አንገባም ብለው በመቃወም የተወለዱበትን ቦታ ለቀው እየሸሹ መሆናቸው ተገልጿል።
    ይህ በንዲህ እንዳለ በደቡብ ክልል በሚገኙ ከተማዎች የሚኖረውን ህብረተሰብ በመንግስት ላይ እምነት የለህም በሚል ምክንያት፤ በስርአቱ ካድሬዎች እየተደበደበ፤ እየታሰረና የተለያዩ ግፍ እየወረደበት እንደሆነ የገለፀው መረጃው፤ እነኝህ ተበዳይ ህብረተሰብ መፍትሄ ለማግኘት ብለው ወደ ሚመለከታቸው አካላት ብሶታቸውን ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።