ምንጮቻችን እንደገለፁት በደቡብ ክልል ኦሞ
ዞን የሚኖረው መላው ህብረተሰብ በጸረ ህዝብ የኢህአዴግ ጉጅሌ የሚጠራውን
ስብሰባ አንካፈልም በማለት እየተቃወሙ መሆኑን የገለፀው መረጃው፤ ዋናው የመቃወምያ ምክንያትም ኢህአዴግ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮቻችን
የማይፈታ ስርአት ስለሆነ፤ ከስልጣኑ እንዲወርድ እንጅ ስልጣን ላይ እንዲቀጥል ታስቦ በሚደረገው ስብሰባ ላይ አንሳተፍም የሚል አቋም
በመያዝ መሆኑን የተገኘው መረጃ አብራርቷል።
መረጃው ጨምሮ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች በመጪው ምርጫ ላይ መመረጥ አንችልም
በማለት ተስፋ ስለቆረጡ ለተለያዩ ልማታዊ ስራዎች ተብሎ የተመደበውን ገንዘብ ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ ወደ ግል ጥቅማቸው እያዋሉት
እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።