በደረሰን መረጃ መሰረት በሰሜን እዝ በተለያዩ ክፍለጦሮች የሚገኙ የሰራዊት
አባላት ኢህአዴግ ምርጫውን ስላሸነፈና የግንቦት 20 በዓልን ለማክበር በሚል ከሰራዊቱ ፍላጎት ውጭ በሆነ መንገድ ከእዙ ወታደራዊ
ክበብ ለሁሉም ክፍለጠሮች የሚሆን 12,625,836 ብር ወጪ አድርገው እንደተጠቀሙበት ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ያለምንም ፈቃድ ከእያዳንድ ወታደር ከግንቦት ወር ደመወዙ 125 ብር
እንዲቆረጥ የተደረገውን ኢ-ፍትሓዊ አሰራር መላው የሰራዊቱ አባላት
መቃወማቸውንና ብሶታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስታውቋል።