በምስራቅ እዝ የሚገኙ 2 ክፍለጠሮች፤ በኢትዮጵያ
ሶማሌ ክልልና ጦላይ አካባቢ በዙርያ ጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት የሰራዊቱ አባላትን በማሰባሰብ ስርዓቱ ያለ ሰራዊቱ ፍላጎት
ወደ ሶማሊያ እንዲሄዱ ማድረጉን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
የኢህአዴግ አመራሮች ሌተቀን ሃገራችን ውስጥ ሰላም ሰፍኗል እያሉ በተለያዩ
የሚድያ ማሰራጫዎች ቢናገሩም በየአቅጣቻው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ ካሉት ድርጅቶች ከሚደርስባቸው ጥቃት ለመከላከልና ሰላም በማስከበር
ስም በየቦታው እየሄደ ህይወቱን እያጣ ያለው ጭቁን ወታደር እጅግ በርካታ መሆኑን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።