Tuesday, June 16, 2015

ቀፀላ ሻረው የተባለው የስርዓቱ ካድሬና የመራኛ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበረ ለሴፍትኔት ተብሎ የተመደበውን 2,867,284 ብር ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው ተገለጸ።



በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን መራኛ በተባለው ቦታ የወረዳው አስተዳዳሪ የሆነው ቀፀላ ሻረው የተባለ ካድሬ ከገጠር ቀበሌና የግብርና ሙያተኞች ጋር በመተባበር ያልተጠቀሙ የሰዎችን ስም ዝርዝር ፌርማ በማዘጋጀት 2,867,284 ብር መዝረፉን ሰሞኑን በተደረገ የአመቱ የበጀት ሂሳብ ቁጥጥር ላይ ሊታወቅ ተችሏል።
    ምንጮቻችን አክለው እንደገለፁት ይህን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እስካሁን በህግ የጠየቀው የመንግስት አካል እንደሌለና በስብሰባ ላይ ግን የወረዳው የፋይናንስ ሰራተኛ የሆነው ባየ አመነ ገንዘቡን እንደወሰደው በሚያጋልጥበት   ሰዓት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ስልጣኑን ተገን በማድረግ እስርቤት ውስጥ እንዲገባ እንዳደረገው የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።