Sunday, June 21, 2015

በመቐለ ከተማ ልዩ ስሙ ዓዲ-ሓ በመባል የሚታወቀው አካባቢ የሚኖሩ አብዛኛዎችሁ ለዓረና/መድረክ በመምረጣቸው የተነሳ በህወሓት ካድሬዎች ጫና እየደረሰባቸው እንዳሉ ታወቀ።



የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በመቐለ ከተማ የዓዲ-ሓ አካባቢ ነዋሪዎች ግንቦት 16 2007ዓ/ም  በተካሄደው የይስሙላ ምርጫ ላይ በርከት ያለ ህዝብ ለተቃዋሚ ድርጅት ዓረና/መድረክ መምረጡን የገለፀው መረጃው በዚህ የሰጉት የወረዳውና የቀበሌው አስተዳደሮች በስልጣን ላይ ያለውን ህወሓት/ኢህአዴግ ለሚቃወሙ ዜጎች ፀረ መንግስት ቀስቅሳችኃል በሚል ምክንያት ተጠቅመው ጥብቅ ክትትልና የተለያዩ ችሮችን እያወረዱባቸው እንደሚገኙ ተገለጸ።
መረጃው በማስከተል የህወሓት ካድሬዎች ለዓረና/መድረክ መርጠዋል ያሉዋቸውን ነዋሪዎች ከቀበሌ የሚሰጥ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች እንዳያገኙና ለማህበራዊ አገልግሎት የሚሆን እንዳይገዙ እየከለከሉዋቸው እንደሚገኙና ይህ ፀረ ዴሞክራሲ አካሄድ ደግሞ በመቐለ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተፈጸመ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።