Saturday, July 4, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ውጤት ተከትሎ ቅሬታዎች በመከሰቱ ምክንያት ህዝቡ አመፅ እንዳያስነሳ ስጋት ያደረበት የኢህአዴግ ገዢ ስርአት በከተማዋ ውስጥ በርካታ ታጣቂዎች ማሰማራቱን ተገለጸ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የኢህአዴግ ገዢ ስርአት ግንቦት 16 /2007ዓ/ም የተካሄደው የይስሙላ ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ ኢህአዴግ አብላጫ የህዝብ ድምፅ አግኝተዋል፤ በመላው የሃገራች ክልሎች ሞቶ በሞቶ ማሸነፉ ሰኔ 15 2007ዓ/ም ካዋጀ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ድምፃችን ተጭበርብረዋል እንጂ ለአምባገነኑ የወያነ-ኢህ አህአዴግ ስርአት አልመረጥንም በማለት እስከ አሁን ድረስ ቅሬታውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
    በከተማው ህዝብ ዘንድ በሰፊው ተቀጣጥሎ ያለውን ህዝባዊ ቅሬታ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ተሸጋግሮ ከስልጣን ወንበራቸው እንዳያስነሳቸው የሰጉት የኢህአዴግ ብዱን  መሪዎች ከህዝቡ ያጥቱን ይልንታ በጠመንጃ ሃይል ለማግኘት ሲሉ ለሆዳቸው ያደሩት ታጣቂ ሃይሎች በማሰማራት ነዋሪው ህብረተሰብ የት ነበርክ? ወዴት ነህ በማለት እያስፈራሩትና እያስጨነቁት እንደሚገኙ መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።