በትግራይ
ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሸራሮ ከተማ ህዳር 17 2008 ዓ/ም በጠሩት ስብሰባ ላይ ለተገኘው ህዝብ መድረኩ እየመሩት የነበሩትን
አስተዳደሮች “የመለስ አደራ አናኮላሽም፤ የመለስ ቃል እንከተል" የሚል መፎክር አንግበው በስብሰባው ውስጥ
እንዳስተጋቡት የገለፀው መረጃው። ተሰብሳቢው ህዝቡ በበኩሉ ራሳችሁ አክብሩት እንጂ እኛ የሞተውን ሰው አንከተልም ያላቸው ሲሆን
በተለይ ደግሞ ከተሰብሳቢዎቹ ቄስ ገብረመድህን ታደሰ የተባሉት ወገን ራሳችሁ ያበላሻችሁትን አስተዳደር እኛን ምን አድርጉ ነው
የምትሉን በማለት አማርረው እንደተናገሩ ምንጮቻችን ከቦታው ጨምረው አስረድቷል።
በመጨረሻም መረጃው ተሰብሳቢው ህዝብ ለመድረክ መሪዎቹ አስተዳደራቹ
ሌባ ፖሊሳቹ ሌባ ፍርድ ቤታችሁ ሌባ ስለ ሆነም እኛ ለምንድ ነው የመለስ ቃል እናከብራለን እያልን የምንፎክረው ጊዜ አይደለም
ያለነው በተቃራኒው በአስተዳደራችሁ ምክንያት መጥፎ ኑሮ እንድናሳልፍ ተገድደናል እንዳሉዋቸው ለማወቅ ተችሏል።