Saturday, December 12, 2015

በፀገዴ ወረዳ ዳንሻ ከተማ በህዝብና አስተዳዳሪዎች ላይ በተደረገው ሰብሰባ አስመሳይ ግምገማ በመሆኑ የተነሳ ህዝቡ እንዳልተቀበለው በምንጮቻችን መረጃ ሊታውቅ ተችሏል።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ምዕራባዊ  ዞን በዳንሻ ከተማ በህዳር 14 2008ዓ/ም የህዝብና የአስተዳደሪዎች ተብሎ የተደረገ ሰብሰባ አሰመሳይ ግምገማ በመሆኑ በህዝብ ተቀባይነት እንዳላገኘ ከገለፁ በዉኃላ በዚህ መሰረት ተሰብሳቢው ህዝብ እነዚህ ሰብሰባውን ለሚመሩ አካላት ለእኛ አድስ ነገር ለታስተምሩን ሰለ አልቻላችሁ፣ ከአሁን በፊት በርካታ ግምገማ እየተካሄደ በአመራሮቹ ላይ የሚመጣ ለውጥ ሳይሆን በተቃራኒ የገዢው ደርጅትን ደጋፊና ጥላትን ለማውቅ ተብሎው ለእነዚህ አስተዳዳሪዎች ለገመገመ ሰው በመርፊ ቀዳዳ ለማየትና ለመከታተል የተጠቀሙት ስልት ነው በማለት እንደተናገሩ ለማውቅ ተችሏል።
  መረጃው በማስከተል እንዳስረዳው በዚህ እየተካሂደ ባለው ሰብሰባ ላይ አንናገርም አንገመግምም በማለት  ህዝቡ ለቀረበው የመውያያ አጀንዳ ሰለ አጣጣለው እነዚህ መደርክ አመራሮች የሆኑ አስተዳዳሪች ከመደረኩ በተደጋጋሚ እያቀረቡት ያለው አስልቺ መልስ ሳይወጡ መልካም አስተዳደር ለማንገስ ተነስተናል የሚል ሃሳብ ቢያቀርቡም ህዝቡ ግን ፓሊሲያችሁና አስተዳደራችሁ ለይታችሁ በማውቅ በተግባር የተሰኘ አይደለም አንቀበልም ሲሉ በመድርኩ ላይ ኣማርረው  ከተናገሩ ግለስቦች የተወሰኑ  ለመግለፅ ያህል ሚልሻ ማርሻ ገ/ሂር 'ና እንግዳቸው ተሰማ የተባሉ መሆናቸው ታወቀ።