Pages

Tuesday, December 8, 2015

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች በወረዳው ኣስተዳዳሪዎች በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ገለፁ።



   ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣውላዕሎ  ወረዳ ኣይነ  ኣለም ቀበሌ ማይ ትዋሩ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለፁት ‘የወረዳው ኣስተዳዳሪዎች በደል ሰለሚያደርሱብን  መልካም ኣስተዳደር ኣጣን፤ ሙስና እየበዛ ነው፣ፍትህ በቤተሰብ  ሆነ፤ የሚሉና ሌሎችም የህዝብ ኣቤቱታዎች መልስ እንዲያገኙ በማሰብ  በህዳር 6 2008 ዓ/ም የስርኣቱ ወኪል ወደ ሆነችው ድምፂ ወያነ ባቀረቡበት ወቅት ፤  የወረዳው ሓላፊዎች  በበኩላቸው  ለምንድነው? እኛን ሳትነግሩ ወደ ሚድያ  መሄድ ቸኮላችሁ? በማለት ወደ  መኖርያ ቤታቸው በመሄድ እንዳስፈራርዋቸውና ለሌሎችም ደግሞ ከስፍትኔት ስራ  እንዳገዷዋቸው  ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃዎቹ ጨምሮው እንደገለፁት የህዝቡን  ኣቤቱታ  ሰምቶ ኣውንታዊ ምላሽ የሚሰጥ  ኣካል  እንደሌለና  በተቃራኒው በወረዳው የፀጥታ ሓላፊዎች ዛቻና ማስፈራርያ እየደረሰባቸው መሆኑንና በዚህ ሳቢያም ህዝቡ ዋስ ሊሆኖው የሚችል ኣካል በማጣቱና  የድርቁን ሁናቴ ተጨምሮበት  በከባድ  ጭንቀትና ስጋት እንደሚገኝ  ተገለፀ።