Pages

Tuesday, December 8, 2015

በዚህ ሳምንት አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርአት በመቃወም በርከት ያሉት ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ተቀላቀሉ።



የተዛባው የኢህአዴግ የአስተዳደር ፖሊሲ በመቃወም ወደ ትህዴን ከተቀላቀሉት ብዛት ያላቸው ወጣቶች የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል።-
1.  ወጣት ፍሻለ በየነ ከትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን ላእላይ አድያቦ ወረዳ ዕጉብ ቀበሌ
2.  ሓየሎም መኮነን ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ስሑል ቀበሌ
3.  አብርሀት ፍትዊና ሰላም ደስታ ከምስራቃዊ ዞን ኢሮፕ ወረዳ ዓገረ ለኹማ ቀበሌ
4.  ፀጋይ አብርሃ ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን ላእላይ አድያቦ ወረዳ ስዓዲ ክልተ ቀበሌ
5.  ገበረ ህይወት በየነ ከማእከላዊ ዞን መረብ ለከ ወረዳ ምሕቛን ቀበሌና ሌሎችም የሚገኙባቸው ሲሆኑ።
ወጣት ፍሻለ በየነ በሰጠው መረጃ መሰረት፣- የገዢው የኢህአዴግ ስርአት አስተዳደሮች በሙስና የተጨማለቁ ሰለሆኑ አገልግሎት ፍልገህ ወደ ተለያዩ የመንግስት መስራ ቤቶች በምትሄድበት ጊዜ የምትፈልገው ለማግኝት ጉቦ በመስጠት ካልሆነ በስተቀር በደቂቃዎች ሊፈታ የሚገባውን ስራ ቀን በቀን በመቁጠር በመንከራተት ጊዜህን የምትፈጅበት ሁኔታ ነው የሚፈትሩልህ በማለት አስረድቷል።
ወጣት ፍሻለ አክሎ በማስረዳት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጠው የዕጉብ ቀበሌ አስተዳዳሪ የሆነው አቶ ገበረአበዝጊ ኪዳነ በሚጠይቅበት ጊዜ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ካልሰጠህን በስተቀር መታወቂያ አልሰጥህም በማለት ስለከለከለኝ እለታዊ ኑሮየን ለማሻሻል ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሼ ለመስራት በዙ ተግዳሮቶች አጋጥሞብኛል ሲል በመናገር።
በመጨረሻም ወጣቱ እንዳለው፣- በዕጉብ ቀበሌ የሚገኙ አስተዳደሮች ነዋሪውን ህዝብ ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ምክንያት እየፈጠሩ በታጠቁ ሃይሎች እንደሚዝዋቸውና እንደሚያንገላትዋቸው ከዛም ባለፈም የማይፈልጉት ሰው ህጋዊ ባልሆነ ቦታ በየቀኑ አስረው በሚኒሻ እንደሚያስጠብቅዋቸው አስታውቋል።