በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን የሚገኙ ወጣቶች በኢህአደግ ታጣቂዎች ተይዘው እየጠፉ መሆኑን የገለፀው መረጃው፣ ከእነዚህ
ወስጥ ሸመልስ አሰፋ፣ ታከለ አሰፋ ታረፈ ኩራዝና ማሙሽ የሚባሉ ወጣቶች የተቃዋሚ ደረጅት አባላት ናችሁ እየተባሉ በስረአቱ ታጣቂዎች ከተወሰዱ በኃላ እስከ አሁን ደረስ የት እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ተገለፀ።
እነዚህ በዚህ ሰረአት
ታፍፈነው የተወሰዱ ወጣቶች በተለያዩ የንግድ ሰራ የሚንቀሳቀሱ የነበሩ ቢሆኑም፣ ይህ ሰረአት ግን በክልሉ ለሚካሂደው ተቃውሞ ህዝብን
ለመስበክ ያለምንም ጨብጥ የተቃዋሚ ደርጅቶች ደጋፊ ናቹ በማለት ወደ ማይታወቅ ቦታ እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል፣፣