በምንጮቻችን መረጃ መሰረት፣ በትግራይ ምስራቃዊ
ዞን ጋንታ አፈሹም ወረዳ ለወሃ አገልግሎት ተብሎ ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ የተወሰኑ አመራሮች ለግል
ጥቅማቸው እያወሉት እንድሆኑ የገለፀው መረጃው እነዚህ የህዝብ ገንዘበን በማጥፋት ከተሰማሩ አመራር ወስጥ ገዛኢ የተባለ የወረዳው የወሃ መዕደን ሃላፊ 59ሺ አሸናፊ የተባለ
የወረዳው የወሃ መኣደን ምክትል ሃላፊ 49 ሺ እንዲሁም ክብሮም ህደጉ የሚባለውን ገንዘብ ያዥ እና ሌላ ክብሮም የሚባሉ 4 ግለሰዎች
ለወሃ ኣገልግሎት ተብሎ ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ኣዉለዋል የሚል ኣቤቱታ ከህዝብ ሰለ ቀረበ በእስርቤት ኣንደገቡ
ለማወቅ ተችለዋል።
እንደዚህ አይነት የህዝብና የአገር ገንዘብ የማጠፋፋት ስራ በምሰራቃዊ ዞን ባለስልጣናት የተለመደ ሲሆን፣ በሌሎች
ክልሎችና ዞኖች የሚገኙ ሃላፈዎችም ስልጣናቸውን ተጠቅመው በተገለፀው የስርቅ ስራ መሰማራት በተደጋጋሚ የሚታይ ተግባራቸው መሆኑ ሊታወቅ ተችሏል፣፣