Sunday, January 31, 2016

መንግስት የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ለማስፋት የሚለውን አዲሱ ማስተር ፕላን እቅድ እንደሚያቆመው ቢገልፅም እንኳ። በኦሮሚያ ክልል ግን ተቃውሞውን እየቀጠለ እንደሚገኝ ተገለፀ።



     በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባንና አካባቢውን ለተሳሰር በሚል የወጣውን እቅድ፣ ኢህአዴግ እንደሚያቆመው ከገለፀ በኋላ፣ ይሁን እንጂ ህዝቡ መግለጫውን ለማዘናጋት ነው እንጂ በስርአቱ ታመኖበት ዘላቂ ሊሆን አይችልም በሚል በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ተቃውሞውን በመቀጠል ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

      የተቃውሞውን እንደ አጋርነት፣ ባለፈው እሁድ በምስራቅ ወለጋ ኡጆ ከተማ በአንድ የሰርግ ስነ ስርአት ላይ በዘፋኞችና ተወዛዋዦች መካከል የተቃውሞ ድምፅ ለማቆም የኢህአዴግ ስርአት ፀጥታ ሃይሎች በወሰዱት የሃይል አርምጃ፣ አንድ ወጣት አንደሞተና ሌሎች 3 ደግሞ እንደቆሰሉ አንድ ስማቸውን ለመግለፅ ያልፈለጉት የአይን ምስክር ከቦታው ለሚዲያዎች በሰጡት ሃሳብ ገልፀዋል።

    የሞተውን ወጣት ዘሪሁን ጂሬኛ የተባለ ሲሆን በነቀምቴ ሆስፒታል ከሞተ በውሃላ ሬሳው ወደ ኡርጆ ተወስዶ እንደተቀበረ የተገኘው መረጃ ጨምሮው አስረድቷል።



No comments:

Post a Comment