Sunday, April 17, 2016

በስሉልታ ከተማ የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከአካባቢው ወጣቶች ጋር እየተጋጩ መሆናቸዉን የደረሰን መረጃ አመለከተ።



   ከአዲስ አበባው ቤተ መንግስት 28.4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሱሉልታ ከተማ፣ በአካባቢው የሚነሩ ወጣቶች ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ማፋጠጣቸው የደረሰን መረጃ አመልክተዋል የሱሉልታ ወጣቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ በኢ-ዴሞክራስያዊ አስተዳደሩ እየገደለ ያለውን የኢህአዴግ  መንግስት በገንዘብ ይደግፋሉ ያሏቸውን የሼህ መሀመድ አላሙዲ 3 መኪኖችን በድንጋይ ሰባብሯል።
  መረጃው አስከትሎ እንደጠቆመው፣ በሱሉልታ ከተማ የሚገኘ አንድ የኤሌክትሪክ ትራንፎርሜሽን መፈንዳቱን ተከትሎ፣ አካባቢው በፌደራል ፖሊሶች በመከበቡ የተነሳ ሕዝቡ ፖሊሶቹን አትወክሉንም፤ ከአካባቢያችን ዞር በሉ በሚል ተቃውሞውን ማሰማቱን ተከትሎ፣ ፖሊሶች ቶክሰዋል በወጣቶች ላይም ዱላ መሰንዘራቸዉ  ታዉቀዋል። አንዳንድ ወጣቶችም አጸፋውን በፖሊሶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን  የገለፀው የደረሰን መረጃ፣ ፖሊሶች ደግሞ በተኩስ የወጣቱን ተቃውሞ ለመበተን ሞክረዋል ተብሏል።
 በተጨማሪም፣ ይህ ተቃውሞ እየተደረገ ባለበት ወቅት በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆኑ መኪኖች፣ በድንጋይ ሲደበደቡ የሦስቱም መኪኖች መስታወቶች መርገፋቸው ተሰምቷል።
በሌላ በኩልም በሰበታ የሁለተኛና የፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ወታደሮች እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች ያስረዳሉ።

No comments:

Post a Comment