Sunday, February 8, 2015

በህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አመራር የተማረሩ የቃፍታ ሁመራ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ አንወስድም በማለት እንደተቃወሙ ለማወቅ ተችሏል፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በቃፍታ ሁመራ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በረከት አደባይ ራውያን ባዕኸርና ሌሎችም ቀበሌዎች የሚኖር ህዝብ በአካባቢው ካድሬዎች የቀረበላቸው የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ የሚል ጥሪ እኛ የእርሻ መሬታችንን በመንግስት ተቀምተን እስከ ቤተሰቦቻን በረሃብና በጥም እየተሰቃየን ስለምንገኝ የምርጫ ካርድ አንወስድም በማለት እምቢታቸውን እንደገለፁ ታውቋል።
መረጃው ጨምሮም እኒህ ነዋሪዎች ምንም እንኳን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ባይመርጡም የምርጫ ካርድ ወስደው ሌሎችን ተቃዋሚዎችን የማይመርጡበትን ምክንያት ሲገልፁ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ በህዝብ ባይመረጥም እንደልማዱ ድምፅ ሰርቆም ቢሆን ስልጣን ላይ መቆየቱ ስላማይቀር ብንመርጥም ባንመርጥም ትርጉም የለውም ማለታቸውን አብራርቷል።